『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2026 DW 政治・政府
エピソード
  • DW Amharic የግንቦት 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    2026/05/31
    የጋምቤላ ክልል ፖሊስ “የተለየ የይለፍ ፈቃድ ካልተሰጠ በቀር” ማንኛውም ተሽከርካሪ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት መንቀሳቀስ እንደማይችል አስታወቀ። በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አምስት ሕሙማን ከኢቦላ ማገገማቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ። ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር የኑክሌር የጦር መሣሪያ ላለመስራት መስማማቷን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ። የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ግን “የኢራናውያን መብቶች መከበራቸውን ሳናረጋግጥ አንዳች ሥምምነት አናጸድቅም” ብለዋል።
    続きを読む 一部表示
    8 分
  • የግንቦት 22 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና
    2026/05/30
    የዛሬው የዓለም ዜና፤የአማራ ፋኖ የጣለው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ የምርጫ ሥራዉን ስለማስተጎጎሉ የደረሰው መረጃ እንደሌለ ምርጫ ቤርድ ማስታወቁ፣የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የኢቦላ ወረርሽን ወደተቀሰቀሰባት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ማምራታቸውን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ መስጠቷን፣ በጀርመን የሙኒክ አውሮፕላን ማረፊያ አጠራጣሪ ድሮን መታየቱን ተከትሎ ለአጭር ጊዜ በረራ መቋረጡን አሜሪካ ስምምነት ላይ ካልደረሰ በኢራን ጦርነቱን እንደገና ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን መግለጿን፣እንዲሁምሩሲያ፤ በአርሜኒያ የሚገኙ አምሳደሯን መጥራቷን አካቷል።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2026/05/29
    ከአማራ ክልል መንገደኞችን ጭኖ ትናንት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ አውቶብስ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ። ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የተነሳውን እሳት በመለኮስ የተጠረጠሩ ስምንት ተማሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የኬንያ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በኤቦላ ተሐዋሲ ለተያዙ የአሜሪካ ዜጎች አግልሎ ማቆያ የማዘጋጀት እቅድን በጊዜያዊነት አገደ። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለገባችበት ውዝግብ ለታሰበው የሰላም ስምምነት ከቃል ይልቅ ተግባር እንደምትፈልግ አስታወቀች።
    続きを読む 一部表示
    11 分
adbl_web_anon_alc_button_suppression_c
まだレビューはありません